“አባቴ ፊት ደፈሩኝ።
ድምጽ እንኳ ማውጣት በጣም ፈርቼ ነበር።
ሁለታችንንም እንደሚገድሉን ዛቱብን”
– የ24 ዓመቷ የትግራይ ሴት
“ወደቤታችን ዘልቀው ገብተው መዝረፍ ጀመሩ። እዛ ላይ ማቆም አልፈለጉም።
አስገድደው ደፈሩኝ።
ወንድሜ እኔን ለመከላከል ሊደባደብ ሞከረ፤ ግን ሊታደገኝ አልቻለም።
ደፍረውኝ ሲያበቁ ወደ ውጪ አውጥተው ተኩሰው ገደሉት”
– የ21 ዓመቷ የትግራይ ሴት
በኢትዮጵያዋ ትግራይ፣ ጭካኔ የተሞላበት የሠራዊት ትብብር፡ አስገድዶ መድፈረ እንደ ጦር መሳሪያ
ዲሴምበር 13፣ 2022 • በሉሲ ካሳ
“አባቴ ፊት ደፈሩኝ። ድምጽ እንኳ ማውጣት በጣም ፈርቼ ነበር። ሁለታችንንም እንደሚገድሉን ዛቱብን” ትላለች በአሁኑ ወቅት በሱዳን ቃዳሪፍ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የምትኖረው የ24 ዓመቷ የትግራይ ተወላጅ ስምረት*።
በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የአማራ እና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባት ሁመራ ከተማ ትኖር ነበር። ጥር 2013 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲፈጸምባት ሁመራ እና የተቀረው ትግራይ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት፣ በጎረቤት ክልል የአማራ ሚሊሻዎች እና በኤርትራ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ነበሩ።
በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በሚመራው ገዢው ፓርቲ እና ትግራይን እያስተዳደረ ባለው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል ለወራት ውጥረት ነግሶ ቆይቶ ጥቅምት 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ህወሓት በፌደራሉ መንግሥት ላይ አመጸ። ጥረታቸው ከሞላ ጎደል አልተሳካም፤ ከኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት እና አጋሮቹ ጋር ለጥቂት ሳምንታት ጦርነት ካከሄዱ በኋላ ወታደሮቻቸው አካባቢውን እንዲለቁ ተደርገዋል።
የትግራይ ክልል ከየካቲት መጨረሻ እስከ ሚያዚያ አጋማሽ 2013 ዓ.ም. በማዕከላዊ መንግሥቱ ቁጥጥር ሥር በነበረችበት ወቅት በክልሉ የጤና ተቋማት ከ1ሺህ 288 በላይ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች መመዝገባቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። ይሁን እንጂ አብዛኛው ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት አለመሄዳቸውን ለአምነስቲ ተናግረዋል፤ ስለዚህ ይህ አሃዝ የሚያሳየው በግጭቱ ውስጥ የተከሰቱ ጥቂት የአስገድዶ የመድፈር ክስተቶችን ነው። ዘ ሴንተር ፎር ኮላቦሬቲቭ ኢንቨስቲጌቲቭ ጆርናሊዝም (ሲሲአይጄ) በኢትዮጵያ ጾታዊ ጥቃቶችን የተመለከቱ ተጨማሪ ማስረጃዎችን አምነስቲን ቢጠይቅም ድርጅቱ ግን ማቅረብ አልቻለም።
በዚህ ምርመራ ላይ ሲሲአይጄ በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ወራት የትግራይ ጤና ቢሮ ኃላፊ ለነበሩት ዶ/ር ፋሲካ አምደስላሴ ቃለ መጠይቅ አድርጓል። እርሳቸው እንደሚሉት ቢሯቸው ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. (የጦርነቱ ጅማሮ) እስከ ሰኔ 3/2013 ዓ.ም. ድረስ 1ሺህ 772 ጾታዊ ጥቃቶችን መዝግቦ ተቀብሏል።
እአአ 2021 ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች፣ የአማራ ሚሊሻ አባላት እና/ወይም የኤርትራ ወታደሮች አስገድዶ መድፈር ስለመፈጸማቸው ሪፖርት የተደረጉባቸው አካባቢዎች።

ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች የተፈጸሙባቸው ሰዎች ቁጥር ጨምሮ ለሕክምና ወደ ሆስፒታሎች መምጣታቸው የሚያሳየው እያስተዳደሩ የነበሩት ወታደሮች መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ ሴቶችን እየደፈሩ መሆኑን ነው። ከዚያ በኋላ ማስረጃዎች መውጣት የጀመሩት በመገናኛ ብዙሃን፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እና በተባበሩት መንግሥታት በተመሠረተው ኮሚሽን ታኅሣሥ 2014 ላይ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት አንዳንድ ወታደሮቹን በግጭቱ ውስጥ በአስገድዶ መድፈር እና በሌሎች የጦር ወንጀሎች ተጠያቂ አድርጊያለሁ ብሏል፤ ይሁን እንጂ የተፈጸመውን የጾታዊ ጥቃት ስፋት እና የተፈጸመበትን ስልታዊ ሁኔታን ያሳንሳል። “በርካታ ወታደሮቻችን የዕድሜ ልክ እስራትን ጨምሮ ጠንካራ፤ ጠንካራ ቅጣቶች ተጥሎባቸዋል” ሲሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነሐሴ 2013 ዓ.ም. ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ክስ የተመሠረተባቸው ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩት የአማራ ክልል ሚሊሻ አባላትን ይጨምር እንደሆነ ያሉት ነገር የለም። ሲሲአይጄ ከበርካታ የጥቃቱ ሰለባዎች እና ከዓይን እማኞች ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረገ ሲሆን የፌደራል መንግሥት ወታደሮችን ጨምሮ የአማራ ሚሊሻ አባላት እና የኤርትራ ወታደሮች በምዕራብ ትግራይ ለተፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተጠያቂ ተደርገዋል።
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በመንግሥት ወታደሮች የተፈጸመውን ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ስፋትንም አሳንሰዋል። እርሳቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግሥት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ መመርመሩን እና አስገድዶ መድፈሩ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተከናውኗል መባሉን እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። “የተጋነኑ ሪፖርቶች አሉ- በጣም የተጋነኑ እና ያልተረጋገጡ” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት በኢትዮጵያ ከሌሎች በደሎች በተጨማሪ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች “በሚያስደነግጥ ስፋት” መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ከኮሚሽኑ ሪፖርት በፊት የፌደራል መንግሥቱ የሴቶች ሚንስትር ፊልሰን አብዲ፤ የመንግሥት ወታደሮች እና አጋሮቹ የፈጸሙትን በደል የሚያሳይ የሚንስትር መስሪያ ቤታቸው ግኝት ይፋዊ በሆነ መልኩ ለማድበስበስ ተሞክሯል በማለት ከስራቸው በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል።
በደል ፈጻሚዎቹ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚዋጉት ብቻ አልነበሩም። ሲሲአይጄ ማረጋገጥ እንደቻለው የትግራይ ተዋጊዎችም በዚህ ውስብስብ በሆነ ግጭት ውስጥ በሌሎች አካባቢዎች አስገድዶ መድፈርን የጦር መሳሪያ አድርጎ ከመጠቀም ጋር ሊስተካከል የሚችል ጥሰቶችን ፈጽመዋል።
በሁሉም ወገን ያሉት እያንዳንዱ ጥቃት አድራሽ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተጠያቂ ሳይሆኑ፤ ጥቃት የተፈጸመባቸው ከ13 ዓመት ታዳጊ እስከ አዛውንት እናቶች ድረስ ያሉት ላይ የማይሽር ጠባሳ ጥሎ አልፎባቸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ጥቅምት 2015 ዓ.ም. ማጠናቀቂያ ላይ የሰላም ስምምነት መፈረማቸውን ተከትሎ ግጭት የቆመ ቢመስልም፤ የተደረሰው ስምምነት አስገድዶ ደፋሪዎችን ተጠያቂ ስለማድረግ እና የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎችን ስለመርዳት አንዳችም ነገር አይልም።
የካቲት 2013 ዓ.ም. ከሴት ልጇቿ ጋር በአንድ ላይ በአማራ ሚሊሻ አባላት እንደሆኑ በምትገምታቸው ሰዎች የተደፈረች በ50ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ እናት፤ “ሕይወታችን ተበለሻሽቷል” ትላለች።
“ከዚህ ቀደም የነበረን አይነት ማሕበራዊ ሕይወት የለንም” ብላለች ወደ ረዥም ዝምታ ውስጥ ከመግባቷ በፊት።
“ጌጣ ጌጡን ከወሰዱ በኋላ ሊወጡ ነበር፤ ግን ሦስቱ አስገድዶ የመድፈር ሃሳብን አመጡ።
እኔን የፈለጉትን እንዲያደርጉ ነገር ግን ሴት ልጆቼን እንዳይነኩ ለመንኳቸው።
የ25 እና የ19 ዓመት ሴት ልጆቼን እየተፈራረቁ ከደፈሩ በኋላ ወደ እኔ ዞሩ።”
– የ52 ዓመት የትግራይ እናት
ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ያልሆኑ በደል ፈጻሚዎች
ከሌላኛዋ የጦርነቱ ተሳታፊ ኤርትራ አንጻር የኢትዮጵያ ጥሰቶችን አለማመን እና ተጠያቂዎችን በስፋት ለፍርድ አለማቅረቧ ‘የተሻለ ፍትሕ’ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በትግራዩ ግጭት የኤርትራ ወታደሮች አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀማቸውን ብዙ ማስረጃዎች አሳይተዋል።
ሲሲአይጄ በዚህ ምርመራ ካነጋገራቸው 13 የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች መካከል አምስቱ አስገድደው የደፈሩን የኤርትራ ሠራዊት አባላት ናቸው ያሉ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ተጠያቂ ያደረጉት የኢትዮጵያን ወታደሮች ነው። የኤርትራ ሠራዊት “የአፍሪካዋ ሰሜን ኮሪያ” በመባል የምትጠራው ኤርትራ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ ተጠያቂ አልሆነችም።
ስምረት ጥቃት ያደረሱባት የኤርትራ ሠራዊት የደንብ ልብስ የለበሱ መሆናቸውን ትናገራለች። “በመጀመሪያ ደረጃ ማንነታቸውን ለመደበቅ ጥረት አላደረጉም። እራሳቸውን እንደ ኤርትራውያን አድርገው ነው የቀረቡት” በማለት ታስረዳለች።
በእነዚህ ወራት ሁመራን ጥላ የሸሸችው እና በ9 ወታደሮች ተገዳ የተደፈረችው የ17 ዓመት ሴት ልጅ፤ “በግልጽ አስታውሳለሁ . . . አምስት የኤርትራ ወታደሮች ነበሩ” ትላለች።
የተቀሩት 4 ወታደሮች ማንነት ለእርሷ ግልጽ አልነበረም – ድርጊቱ ሲፈጸምባት ሙሉ በሙሉ እራሷን አታውቅም ነበር። “እንደ መጥፎ ሕልም ነበር፤ ማስታውሰው አራት እንደነበሩ ነው፤ አማርኛ (የኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ቋንቋ) ያወሩ ነበር” በማለት ታስታውሳለች።
እርሷ እንደምትለው ጥቃቱ የተፈጸመባት የካቲት 2013 ዓ.ም. ወታደሮቹ ወደ ካምፓቸው እንድታመራ ካዘዟት በኋላ ነበር። “ተኩሰው ይገድሉኛል ብዬ በጣም ፈርቼ ነበር። ስለዚህ ትዕዛዛቸውን ተቀበልኩ። ካምፕ ስንደርስ፤ ልብሴን በኃይል ቀዳደው እየተፈራረቁ በቡድን ደፈሩኝ” ብላለች።
ይህች ልጅ እንደምትለው ከሆነ ሚያዚያ 2013 መጀመሪያ አካባቢ እርሷ እና ሌሎች ከአዲ ጎሹ የተፈናቀሉ ሰዎች ምዕራብ ትግራይ ሁመራ ደረሱ። “አስቆሙን፤ ሌሎቹ እንዲሄዱ ፈቅደው እኔ እንድቆይ አዘዙኝ። ከዛ በአካባቢው ወዳለ ቤት በኃይል አስገቡኝ- የደፈሩኝ የዛን ጊዜ ነው።”
ይህ ከመሆኑ በፊት ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በአዲ ጎሹ አካባቢ ካለ አንድ ቤተ-ክርስቲያን ስትመለስ የነበረች የ31 ዓመት ሴት የኤርትራ ሠራዊት አባላት መሆናቸውን በለየቻቸው 5 ወታደሮች ተተናኩለዋት ነበር።
“እኛ መንደር ውስጥ ነበር መቀመጫቸውን ያደረጉት” ትላለች። “በኃይል ወደ ቤት ውስጥ ካስገቡኝ በኋላ በቡድን ሆነው ደፈሩኝ።”
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ሌሎች ታዛቢዎች የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ በዋነኝነት ጾታዊ ጥቃቶችን ስለማድረሳቸው ጠቅሰዋል። በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አማካይነት የተሰበሰበ የሰብዓዊ መረጃዎች መለዋወጫ ላይ እንደተመላከተው ከተመዘገቡ ጾታዊ ጥቃቶች ከሦስቱ አንዱን የፈጸሙት የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት አባላት መሆናቸውን በስም ይጠቅሳል። በዚህ ሪፖርት ውስጥ የተካተቱት መረጃዎች ለሁሉም ክፍት የሆኑ ስልቶችን በመጠቀም የተሰበሰቡ እና መንግሥታዊ ሪፖርቶችን ያጠቃለሉ ሲሆን በትግራይ የተከሰቱ ጾታዊ ጥቃቶችን በሙሉ ግን መዝግበው አልያዙም።
“ወታደሮቹ (የፌደራል መንግሥት) ቤት ለቤት እየዞሩ የህወሓት ደጋፊዎችን ሲፈልጉ ነበር።
እኔ ደጋፊ አለመሆኔን አስረድቼ የሥራ መታወቂያዬን አሳየዋቸሁ።
በጥፊ መትተውኝ በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ።”
– የ37 ዓመቷ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅጥረኛ
ለአስርት ዓመታት በግጭት ውስጥ የዘለቀው ቂም በቀል
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ከራሱ ክልል ጋር በገባው ጦርነት ተሳታፊ የሆኑት በኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና በህወሓት መካከል ለአስርት ዓመታት በዘለቀው ቁርሾ ምክንያት ነው።
ጉዳዩ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነጻ ለመውጣት ትግል በምታደርግ ጊዜ ይጀምራል። ህወሓት ይህን ትግል ይደግፍ እንጂ ጥምረታቸው ወጥ አልነበረም። ሁለቱ ኃይሎች በአንድ ላይ ሆነው የኢትዮጵያ ሕብረተሰባዊት መንግሥትን 1983 ላይ አሸነፉ። ኤርትራ ተገነጠለች። ይህም ከሌሎች የኢትዮጵያ አመጺ ቡድኖች ጋር ወዳጅነት እንድትመሰረት ያስቻላት ሲሆን፤ ህወሓት ደግሞ በአዲስ አበባ ስልጣን ያዘ።
ኤርትራም ሆነች ትግራይ የኢትዮጵያ አንድ አካል የነበሩ እንደመሆናቸው መጠን ኤርትራ ስትገነጠል የድንበር ጉዳይ ብዙም አንገብጋቢ አልነበረም። ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች በኋላ ግን ኢሳያስ አፈወርቂ ባድመ የተባለው ቦታ ይገባኛል አሉ፤ ህወሓት ደግሞ ይህን ቦታ የግዛቱ አካል አድርጎ ይቆጥረዋል።
ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ጦር ግንባር በማምራት 1992 ላይ ከኤርትራ ጋር በመዋጋት የድንበር ጦርነት ውስጥ ገባ፤ ይህን በቀድሞ አጋሮች መካከል ለዓመታት የዘለቀ ግጭት ቀሰቀሰ።
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል እአአ 2000 ላይ የተፈረውም የአልጀርስ ስምምነት ቀጥተኛ ግጭትን ማስቆም አስቻለ። የድንበር ጉዳዩ ወደ ዘ ሄግ የድንበር ኮሚሽን ተመርቶ ለኤርትራ ተፈረደ። ይሁን እንጂ ህወሓት መራሹ የአዲስ አበባው መንግሥት ግዛቶቹን ለኤርትራ አልፎ ለመስጠት አሻፈረኝ አለ።
ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አሁንም ኤርትራን እየመሩ የሚገኙት ኢሳያስ ከጎረቤት አገር ጋር ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ምክንያትን በማቅረብ ዜጎች አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋሉ።
አሁን ስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በማሻሻላቸው የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል። “የሕግ ማስከበር ዕርምጃ” ብለው በትግራይ የጀመሩት ዘመቻ ወደ ሙሉ ጦርነት ሲሸጋገር የኤርትራ ወታደሮች ጦርነቱን ተቀላቀሉ።
የጦር ሜዳ ውሏቸው ግን የረዥም ጊዜ ፖለቲካዊ ቁርሾ ትንቅንቅ እንጂ የታለመው የሕግ ማስከበር እርምጃ አይመስልም።
ህወሓት ለኤርትራ ጦር ድጋፍ ያደርጋል።
ኤርትራ ነጻነቷን ከኢትዮጵያ አውጃ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ማስተዳደር ጀመሩ።
ኢትዮጵያ በህወሓት የበላይነት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በተባለ ጥምር ፓርቲ በፌደራል መንግሥት አወቃቀር መመራት ጀመረች።
ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ጀመረ።
በህወሓት የበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግሥት ግዛቱን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀረ።
ዐቢይ ምንም እንኳ የህወሓት አባል ባይሆኑም፤ በኢሕአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የሰልጣን እርከን ላይ ሆነው አገልግለዋል።
ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን በመሰለፍ ጦርነቱን ተቀላቀለች።
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ከራሱ ክልል ጋር በገባው ጦርነት ተሳታፊ የሆኑት በኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና በህወሓት መካከል ለአስርት ዓመታት በዘለቀው ቁርሾ ምክንያት ነው።
ጉዳዩ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነጻ ለመውጣት ትግል በምታደርግ ጊዜ ይጀምራል። ህወሓት ይህን ትግል ይደግፍ እንጂ ጥምረታቸው ወጥ አልነበረም። ሁለቱ ኃይሎች በአንድ ላይ ሆነው የኢትዮጵያ ሕብረተሰባዊት መንግሥትን 1983 ላይ አሸነፉ። ኤርትራ ተገነጠለች። ይህም ከሌሎች የኢትዮጵያ አመጺ ቡድኖች ጋር ወዳጅነት እንድትመሰረት ያስቻላት ሲሆን፤ ህወሓት ደግሞ በአዲስ አበባ ስልጣን ያዘ።
ኤርትራም ሆነች ትግራይ የኢትዮጵያ አንድ አካል የነበሩ እንደመሆናቸው መጠን ኤርትራ ስትገነጠል የድንበር ጉዳይ ብዙም አንገብጋቢ አልነበረም። ከኢትዮጵያ ከተገነጠለች በኋላ ግን ኢሳያስ አፈወርቂ ባድመ የተባለው ቦታ ይገባኛል አሉ፤ ህወሓት ደግሞ ይህን ቦታ የግዛቱ አካል አድርጎ ይቆጥረዋል።
ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ጦር ግንባር በማምራት 1992 ላይ ከኤርትራ ጋር በመዋጋት የድንበር ጦርነት ውስጥ ገባ፤ ይህን በቀድሞ አጋሮች መካከል ለዓመታት የዘለቀ ግጭት ቀሰቀሰ።
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል እአአ 2000 ላይ የተፈረውም የአልጀርስ ስምምነት ቀጥተኛ ግጭትን ማስቆም አስቻለ። የድንበር ጉዳዩ ወደ ዘ ሄግ የድንበር ኮሚሽን ተመርቶ ለኤርትራ ተፈረደ። ይሁን እንጂ ህወሓት መራሹ የአዲስ አበባው መንግሥት ግዛቶቹን ለኤርትራ አልፎ ለመስጠት አሻፈረኝ አለ።
ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አሁንም ኤርትራን እየመሩ የሚገኙት ኢሳያስ ከጎረቤት አገር ጋር ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ምክንያትን በማቅረብ ዜጎች አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋሉ።
አሁን ስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በማሻሻላቸው የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል። “የሕግ ማስከበር ዕርምጃ” ብለው በትግራይ የጀመሩት ዘመቻ ወደ ሙሉ ጦርነት ሲሸጋገር የኤርትራ ወታደሮች ጦርነቱን ተቀላቀሉ።
የጦር ሜዳ ውሏቸው ግን የረዥም ጊዜ ፖለቲካዊ ቁርሾ ትንቅንቅ እንጂ የታለመው የሕግ ማስከበር እርምጃ አይመስልም።
ህወሓት ለኤርትራ ጦር ድጋፍ ያደርጋል።
ኤርትራ ነጻነቷን ከኢትዮጵያ አውጃ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ማስተዳደር ጀመሩ።
ኢትዮጵያ በህወሓት የበላይነት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በተባለ ጥምር ፓርቲ በፌደራል መንግሥት አወቃቀር መመራት ጀመረች።
ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ጀመረ።
በህወሓት የበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግሥት ግዛቱን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀረ።
ዐቢይ ምንም እንኳ የህወሓት አባል ባይሆኑም፤ በኢሕአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የሰልጣን እርከን ላይ ሆነው አገልግለዋል።
ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን በመሰለፍ ጦርነቱን ተቀላቀለች።
“አንዳንድ ተጠቂዎች እንዳሉት በቡድን እየደፈሯቸው ወታደሮቹ የትግራይ ደማቸውን እያነጹላቸው እንደሆነ ይነግሯቸዋል”
– ልዋም ገ/ስላሴ፤ የቃድሪፍ የስደተኞች መጠለያ ነርስ
አስገድዶ መድፈር እንደ ጦር መሳሪያ
በርካታ ሪፖርቶች የኤርትራ ወታደሮች ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ጾታዊ ጥቃቶችን እያደረሱ እንደሆነ አሳይተዋል፤ አንድ ክስተት ግን የተፈጸሙትን ወንጀሎች ደረጃ የሚያሳይ ነው።
መጋቢት 2013 ዓ.ም. በ23 የኤርትራ ወታደሮች ተገደው ተደፍረዋል የተባሉ እናት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ሃኪሞች ከሴትየዋ ሰውነት ውስጥ ረዥም ሚስማሮች፣ የፕላስቲክ ስብርባሪዎች እና ጠጠሮች ሲያወጡ ያሳያል።
የኮንጎ ዜግነት ያላት እና ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አስገድዶ መድፈርን እንደ የጦር መሳሪያ አድርጎ እንዲመድብ ጥረት የምታደርገው ቾዉቾዉ ናሜጋቤ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የምትታየው ሴት የደረሰባት ጾታዊ ጥቃት ጥልቀትን ትረዳለች። መልዕክት እየላኩ ነው “ለጠላቶቻቸው መልዕክት እየላኩ ነው – በሴት ሰውነት ውስጥ ድልን ማሳየት እየፈለጉ ነው” ትላለች።
“በኮንጎ መጀመሪያ ላይ ጾታዊ ፍላጎትን ለማርካት መስሎን ነበር። ዘግየትን ግን ለዛ እንዳልሆነ አይተናል” በማለት ናሜጋቤ ታስረዳለች። “እነሱ (ጥቃት አድራሾቹ) በተቻለ መጠን ጉዳት ማድረስን ነው የሚፈልጉት።”
አስገድዶ መድፈር እንደ ጦር መሳሪያ አድርጎ መጠቀምን ለማስቆም የተቋቋመው የዶ/ር ዴኒስ ሙክዌጌ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ካትሪን ኮፕንስ፤ ሰዎችን ለማዋረድ እና የጠላት ኃይልን ለመበታተን የጦር ስልት የሆነውን መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ አድርጎ መጠቀምን ስነ-ምግባር በጎደላቸው ወታደሮች ከሚፈጸም አስገድዶ መድፈር ጋር ያለውን ተመሳሳይ ባህሪ ለይተዋል።
መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ሲውል ከአዛውንቶች እስከ ታዳጊ ልጆች በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ተጠቂ ይሆናሉ ይላሉ። አስገድዶ ደፈሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ በቡድን እና መጠነ ሰፊ በሆነ ደረጃ የሚፈጸሙ ናቸው። ጡት ወይም ሌሎች የጾታ አካል የሆኑ የሰውነት ክፍልን መቁረጥን የሚጨምር በጣም ረባሽ ኃይልም የቀላቀሉም ይሆናሉ።
አስገድዶ መድፈሮቹ ማስቃየትንም ሊያካትቱ ይችላሉ። ደፈራዎቹ ብዙ ጊዜ የሚፈጸሙት የቤተሰብ አባላት ፊት ለፊት ወይም በአደባባይ ነው። እንዲሁም ጥቃት አድራሾቹ ብሔር ተኮር ስድቦችን በመጠቀም ያወርዳሉ።
ኮፐን “እንደ አለመታደል ሆኖ፤ በሁሉም ጦርነቶች ላይ ሊባል በሚችል ደረጃ፤ ጾታን መሠረት ያደረጉት ጥቃቶች እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ይውላሉ፤ ምክንያቱም ፍርሃት በመፍጠር ውጤታማ በመሆኑ እና በሁሉም ባህል ውስጥ ከውርደት ጋር ስለሚያያዝ ነው”
“የስሜት መረበሹ” ይላሉ፤ “ለትውልዶች ያሚያልፍ ነው።”
በሲሲአይጄ ቃለ መጠይቅ ወቅት በትግራይ አብዛኛው ተጠቂ አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ጋር ተመሳሳይ የሆኑ አካሄዶችን ተመልክተናል። በዚህ ምርመራ ላይ ቃላቸውን የሰጡት፤ ወታደሮቹ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ዒላማ አድርገዋል – ከ13 እስከ 65። ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው 13 ተጎጂዎች መካከል 12ቱ በቡድን መደፈራቸውን ተናግረዋል። አራቱ ተጎጂዎች ደግሞ የቤተሰብ አባላቶቻቸው ፊትለፊት በቡድን ተደፍረዋል።
የትግራይ ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አምደስላሴም፤ በኤርትራ ወታደሮችም ይሁን በሌሎች ይፈጸም፤ በዚያ ወቅት በትግራይ የተፈጸመው ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ መልዕክት አለው ይላሉ።
“ሁሉም ማለት ይቻላል በቡድን የመደፈር ክስተቶች ናቸው። ዒላማ የተደረጉት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች ናቸው፤ ከ6 ዓመት እስከ በጣም አዛውንት ሴት። የሃይማኖት ቡድኖች፤ መነኮሳት ሳይቀሩ ዒላማ ተደርገዋል። ጥቃት አድራሾቹ ብሔር ተኮር ስድቦችን ተጠቅመዋል” ይላሉ አምደስላሴ።
“ወሲባዊ ባርነትም ነበር። የወታደሮች ቡድን በደርዘን የሚቆጠሩ ወይም በርካታ ሴቶችን በጦር ካምፕ በኃይል ይዘው በማቆየት በተደጋጋሚ በቡድን ለሳምንታት ከደፈሯቸው በኋላ አውጥተው ይወረውሯቸዋል ወይም በጣም ሲታመሙ ይገድሏቸዋል” በማለት ይናገራሉ።
“አንዳንድ ተጠቂዎች እንዳሉት በቡድን እየደፈሯቸው ወታደሮቹ የትግራይ ደማቸውን እያነጹላቸው እንደሆነ ይነግሯቸዋል” በማለት ለሲሲአይጄ የተናገረችው ደግሞ በሱዳኑ ቃዳሪፍ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎችን የምታክመው ነርስ ሉዋም ገ/ስላሴ ነች።
“በጣም አሮጊት መሆኔን እየነገርኳቸው እንዲተዉኝ ለመንኳቸው።
ግን አላቆሙም”
– የ65 ዓመት የትግራይ እናት
ለተጠያቂነት አማራጮች
የኤርትራ መንግሥት ወታደሮቹ በትግራይ ሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦርነት መሳሪያ አድርገው በመጠቀማቸው ተጠያቂ ማድረግ ቀርቶ አንዳች የሃዘኔታ መልክት እንኳ አላሳየም።
የኢትዮጵያ መንግሥትም አድርጌዋለሁ ካለው ውጪ ተጠያቂነት ለማስፋት ፍላጎቱን አላሳየም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ቡድን በሪፖርቱ መከላከያ፣ አጋሮቹ እና ተገዳዳሪ ኃይሎች ከጦር ወንጀል ጋር ሊስተካከል የሚችል አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ማለቱን ተከትሎ መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ያለውን ቅሬታ አሰምቶ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች በደቡብ አፍሪካ ኅዳር ወር ላይ የሰላም ስምምነት ይፈራረሙ እንጂ፤ አስገድዶ መድፈርም ይሁን የትኛውም አይነት ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ፍትሕ ስለመስጠት የተባለ ነበር የለም።
ይህ ማለት ግን ይላሉ የኮዋሊሽን ፎር ጄኖሳይድ ሪስፖንስ መስራቾች መካከል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ኤዌሊና ኦቻብ፤ ይህ ማለት ግን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመባቸው ሰዎች ለደረሰባቸው በደል ጥፋተኞች ተጠያቂ ሳይሆኑ መቅረት የለባቸውም ይላሉ። መስራች የሆኑበት መስሪያ ቤት የተባበሩት መንግሥታት መረጃዎችን የሚሰበስብበት እና መዝግቦ የሚያስቀምጥበት ስልት እንዲቀይስ እና በተለይ ደግሞ ጾታዊ ጥቃቶች ላይ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ እየጠየቁ ነው።
ኦቻባ ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ተጠያቂነት እና ፍትሕ እንዲኖር የድርጅቶች ጥምራት እንዲኖር እየጠየቁ ነው። “በቅርቡ ከተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች መማር የምንችለው፤ ለምሳሌ በፑቲን (የሩሲዋ መሪ ቭላድሚር) በዩክሬን የተፈጸመው፤ ለፍትሕ እና ተጠያቂነት አንድ ላይ መስራት ብዙ ርቀት እንደሚወስደን ነው። ምንም እንኳ ገና ጅምር ቢሆንም ቢያንስ 18 አገራት በዩክሬን የተፈጸሙ የሩሲያ በደሎችን እየመረመሩ ነው፤ ከዚህ በኋላ ተጠያቂነት ይቀጥላል የሚል ተስፋ አለ።
ኦባቻ ግን ሌሎች አማራጮች እንዳሉ ያስባሉ- ይህም ‘አድ-ሆክ ወይም ሃይብሪድ ትሪቢዩናል’ (ጊዜያዊ ወይም ድብልቅ ችሎት) ማቋቋምን ይጨምራል። አድ-ሆክ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ጊዜያዊ ችሎቶች ሲሆኑ ለአንድ ጉዳይ ተብለው የሚቋቋሙ የዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎቶች ናቸው። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው ለቀድሞ የዩጎዝላቪያ መሪ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት (አይሲቲዋይ) እና ለሩዋንዳ ተመስርቶ የነበረው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት (አይሲቲአር) ነው።
ሁለቱም ችሎቶች በሁለቱ አገራት ክልል ውስጥ በተገደበ ጊዜ ውስጥ በዘር ማጥፋት ወንጀል እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕጎች ከባድ ጥሰት የፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የተቋቋሙ ነበሩ። እንደ ተመድ ከሆነ አይሲቲአር እአአ 1995 ላይ ከተመሠረተ በኋላ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕጎችን የተላለፉ 93 ሰዎችን የለየ ሲሆን ከግለሰቦቹ መካከል ከፍተኛ የጦር አመራሮች፣ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች እና የሃይማኖት እና የመገናኛ ብዙሃን መሪዎች ይገኙበታል።
“የተመድ ኮሚሽን በትግራዩ ጦርነት ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሟል ማለቱ . . . እነዚሀን ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶች ለማቋቋም ወሳኝ እርምጃ ነው። ከዚህ ቀደም በነበሩ ተሞክሮዎች በሩዋንዳም ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶቹ ከመመስረታቸው በፊት ተመሳሳይ ርምጃዎች ነበሩ” ብለዋል ኦቻብ።
ከዚህ በተጨማሪም አገራት ወደ የአገር ውስጥ ፍርድ ቤቶቻቸው ፊታቸውን በማዞር የዓለም አቀፉን የሕግ ተፈጻሚነት መርሆች ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው። ይህም አገራት ወንጀል በየትኛው ቦታ ይፈጸም በደል ፈጻሚን በወንጀል እንዲጠይቁ ስልጣን ይሰጣል ይላሉ። ይህ ብዙውን ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆነው በጣም ከባድ የሆኑ እንደ የዘር ማጥፋት፣ ማሰቃየት እና ሌሎች የጦር ወንጀሎች ሲፈጸሙ ነው።
አንድ የቀርብ ምሳሌ እአአ በ1970ዎቹ በ70 ሰዎች የግድያ ትዕዛዝ ላይ እና በሌሎች ወንጀሎች ላይ የተሳተፈው በቀድሞ የኢትዮጵያ ባለስልጣን -እሸቱ አለሙ- ላይ የተላለፈው ውሳኔ ነው። እአአ 2017 ላይ በኔዘርላንድስ አገር የዕድሜ ልክ እስራት ተላልፎበታል። እአአ 2022 ይግባኝ የጠየቀበት ፍርድ ቤት የተላለፈበትን የዕድሜ ልክ እስራት አጸንቷል።
በተመሳሳይ በቅርብ ዓመታት የስዊዝ ፍርድ ቤቶች በላይቤሪያ የእርስ በርስ ጦርነት የጦር ወንጀሎችን የፈጸሙትን በዓለም አቀፍ ሕጎች ዳኝተዋል። ሰኔ 11 2013 ዓ.ም. የስዊዘርላንድ ፌደራል የወንጀል ፍርድ ቤትበተጠና መልኩ ሰዎችን የገደለ፣ ጾታዊ ጥቃቶችን የፈጸመ እና ሌሎች የጦር ወንጀሎችን በላይቤሪያ ፈጽሟል ያለውን የቀድሞ የጦር መሪ አሊዩ ኮሲአህ በ20 ዓመታት እስራት እንዲቀጣ ፍርዶበታል። ኮሲአህ ይግባኝ ያለ ሲሆን አቤቱታውን ለማድመጥ በአውሮፓውያኑ ጥር 2023 ቀጠሮ ተይዟል።
ኦቻባ በዚህ መርህ መሠረት ክስ መመስረት የሚችሉ ባለሙያዎች ያለው የትኛውን አገር እርምጃ መውሰድ አለባት ይላሉ። ይሁን እንጂ ይህን ተፈጻሚ ማድረግ ላይ ፈተናዎች ሊኖሩ ይችላሉ ይላሉ። “ዐቃቤ ሕጎች ተዓማኒ የሆነ እና ሙሉ የሆነ ማስረጃ ያስፈልጋቸዋል፤ ይሁን እንጂ ትግራይ በኢትዮጵያ መንግሥት ከኢትዮጵያ እና ከተቀረው ዓለም እንድትነጠል ስለተደረገ ይህን ማድረግ አስቸጋሪ ነው” በማለት ያስረዳሉ።
“በቅድሚያ አምስት የሚሊሻ ቡድን አባላት አስገድደው ደፍረውኝ ሄዴ። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ስድስት አባላት ያሉት ቡድን መጥቶ ተመሳሳይ ነገር አደረገ።
ሁሉም የአማራ ሚሊሻዎች ናቸው . . . ወደ ሱዳን እስክሰደድ ድረስ ወደ ሆስፒታል አልሄድኩም።
በሄድኩበት ሰዓት ቫይረሱን ለመከላከል መድሃኒቶችን ለመውሰድ ረፍዶ ነበር። አሁን ኤችአይቪ በደሜ አለ።”
– የ47 ዓመት የትግራይ ሴት
የተጠያቂነት አለመኖር ሌላ ወንጀልን ሲፈጥር
በኢትዮጵያው ግጭት ጾታን መሠረት ያደረገው ጥቃት በትግራይ ብቻ ተገድቦ አልቀረም፤ ጥቃት አድራሾቹም የፌደራል መንግሥት ኃይሎች፣ የአማራ ሚሊሻ እና የኤርትራ ጦር አባላት ብቻ አይደሉም። የትግራይ ኃይሎችም ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ገፍተው በሄዱ ወቅት በክልላቸው ለተፈጸመው ምላሽ ለመስጠት ጾታዊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል።
ከፌደራል መንግሥት የሚንስትርነት ስልጣናቸው በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት ፊልሰን አብዲ፤ ለዋሽንግተን ፖስት ሲናገሩ በትግራይ ክልል የመንግሥት ኃይሎች እና አጋሮቻቸው ለፈጸሙት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠያቂነት ቢኖር ኖሮ ከትግራይ ውጪ የተፈጸሙት ጾታዊ ጥቃቶች ቁጥር በጣም ያነሱ ይሆኑ ነበር ብለዋል።
ሲሲአይጄ በአጸፋ መልክ የተፈጸመው ጥቃት መጠን ማግኘት ባይችልም፤ በአማራ ክልል የሚገኙ ትልልቅ ሆስፒታሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የአስገድዶ መድፈር ያጋጠማቸውን ተጠቂዎች ማከማቸውን ይገምታሉ። ሰብዓዊ ድርጅቶችም የህወሓት ታጣቂዎች ተጠያቂ በተደረጉበት ጥቃቶች በአማራ 26 በአፋር ደግሞ 2 የአስገድዶ መድፈር ክስተቶችን መዝግበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ንፋስ መውጫ በተባለች አንድ ከተማ ብቻ ከ70 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ሲሉ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናግረዋል። አምነስቲ በራሱ ባካሄደው ጥናት ተገደው የተደፈሩ 16 ሴቶችን አግኝቷል።
ምህረት* ህወሓት ባካሄደው አጸፋ ዘመቻ ከተደፈሩት መካከል አንዷ ነች። ስቃይዋ የጀመረው ነሐሴ 26/2013 ዓ.ም. የትግራይ ጦር አባላት ኬኖ ወደተባለችው መንደሯ በመጡ ወቅት ነበር። ቡና ወደምትሸጥበት ቤቷ ስድስት ወታደሮች በኃይል ዘልቀው ከገቡ በኋላ በቡድን ሆነው እንደደፈሯት ትናገራለች።
ለቀጣይ አራት ተከታታይ ቀናት የትግራይ ወታደሮች በቡድን ሆነው አስገድደው መድፈራቸውን ቀጠሉ። እንደ ሃኪሟ ከሆነ ምህረት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባች ሲሆን በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ አድርጋለች።
በሌላኛው የአማራ ክልል መንደር ጭና፤ በርካታ ሴቶች በቡድን የተደፈሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንዷ የ25 ዓመቷ አይናለም ትገኝበታለች፤ እርሷ እንደምትለው ነሐሴ 2/2013 ዓ.ም. በሦስት የትግራይ ተዋጊዎች ተደፍራለች። ለሲሲአይጄ ስትናገር ጾታዊ ጥቃት በሚፈጸምባት ወቅት ጥቃት አድራሾቿ ሲደበድቧት እና እርሷን ለማሸማቀቅ ብሔር ተኮር ስድብ ሲሰድቧት ነበር። ከጾታዊ ጥቃቱ በኋላ ብታረግዝም ጽንሱን ማቋረጥ እንደቻለች ትናገራለች።
“የስሜት መረበሹ ለትውልዶች የሚያልፍ ነው”
– ካትሪን ኮፕንስ፣ የዶ/ር ዴኒስ ሙክዌጌ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር
ተከትሎ የመጣው መዘዝ
በአቧራማው የሱዳን በረሃ በፍጥነት እየተስፋፋ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያዎች ይኖራሉ። ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ በሱዳን ካሉት ስደተኞች ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑት ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከኢትዮጵያ መሆናቸውን ያሳያል።
ከሌሎቹ ስደተኞች በተለየ ሁኔታ፤ እምብዛም ማሕበራዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው አይጥሩም። እንደ እነርሱ ተገደው ከተደፈሩት ጋር ካልሆነ በቀር ስሜት የሚረብሹ ገጠመኞቻቸውን ለማንም ማጋራትን አይፈቅዱም።
ትንሽ ቁጥር ያላቸው ግን ለሲሲአይጄ ተናግረዋል። ምንም እንኳ የዕድሜ ልዩነታቸው እጅግ ሰፊ ቢሆንም ሁሉም ለማለፍ የተገደዱበት ሁኔታ ስሜትን በሚረብሽ መልኩ ተመሳሳይነት አለው።
በአደባይ ከተማ ይኖሩ የነበሩት የ65 ዓመቷ እናት የካቲት 2013 ዓ.ም. በስድስት የሚሊሻ አባላት በቡድን ከተደፈሩ በኋላ ከሚኖሩበት ከተማ ለመሸሽ መገደዳቸውን ይናገራሉ። አማርኛ ይናገሩ ነበር፤ ጥቃት አድራሾቹ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በመወገን በምዕራብ ትግራይ ሲዋጉ የነበሩ የአማራ ክልል ሚሊሻ አባላት እንሆኑ ያምናሉ።
“ቤቴ ውስጥ ነበርኩ። ድንገት የሚሊሻ ቡድን አባላት ወደምኖርበት መንደር መጥተው የቤት ለቤት ፍተሻ እያደረጉ ሰዉን አሸበሩ . . . በጣም አሮጊት መሆኔን እየነገርኳቸው እንዲተዉኝ ለመንኳቸው። ግን አላቆሙም” ሲሉ የሦስት ልጆች እናት እምባ ይተናነቃቸዋል።
ዛሬ ላይ ባሳለፉት መጥፎ አጋጣሚ ብቻ አይደለም የሚያለቅሱት፤ ስለተዋረዱም ጨምር እንጂ። አሁን ላይ አዋቂ የሆኑ ልጆች እናታቸውን ምን እንዳጋጠማቸው የሚያውቁት ነገር የለም። “ምን ብዬ እነግራቸዋለሁ? የተከሰተውን ነገር እኔ እራሱ ሳስበው በጣም የሚያሳፍር ነው።”
የ37 ዓመቷ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኛ ደግሞ ጥቃት የፈጸሙባት እና በሕይወቷ ያስፈራሯት ታገለግለው የነበረው መንግሥት ወታደሮች መሆናቸውን አሁንም ማመን ያቅታታል። እርሷ እንደምትለው ጥር 2013 ዓ.ም. በአዲ ጎሹ ከተማ ቤት ለቤት ፍተሻ ሲያደርጉ ተገዳ እንደተደፈረች ትገልጻለች።
“ወታደሮቹ (የፌደራል መንግሥት) ቤት ለቤት እየዞሩ የህወሓት ደጋፊዎችን ሲፈልጉ ነበር። እኔ ደጋፊ አለመሆኔን አስረድቼ የሥራ መታወቂያዬን አሳየዋቸሁ። በጥፊ መትተውኝ በየተራ እየተፈራረቁ ደፈሩኝ” ስትል የነበረውን ሁኔታ አስረድታለች።
የ21 ዓመቷ ወጣት ደግሞ አሁን ድረስ ለወንድሟ ሞት እራሷን አምርራ ትወቅሳለች። “በእኔ ምክንያት ነው እንጂ አሁን ላይ በሕይወት ይኖር ነበር” ብላለች። ይህች ሴት ክስተቱን ስታስረዳ የአማራ ሚሊሻ አባላት እንደሆኑ የምትገምታቸው ወታደሮች ትኖርበት ወደነበረው አደባይ መጋቢት 2013 ላይ ይመጣሉ።
“ወደቤታችን ዘልቀው ገብተው መዝረፍ ጀመሩ። እዛ ላይ ማቆም አልፈለጉም። አስገድደው ደፈሩኝ። ወንድሜ እኔን ለመከላከል ሊደባደብ ሞከረ፤ ግን ሊታደገኝ አልቻለም። ደፍረውኝ ሲያበቁ ወደ ውጪ አውጥተው ተኩሰው ገደሉት” በማለት ትናገራለች።
የ52 ዓመቷ እናት ደግሞ በአንድ ወቅት እርሳቸው እና ሴት ልጆቻቸው በአደባይ ከተማ የነበራቸውን ሕይወት በሐዘን ስሜት ያስታውሱታል። በአንድ የካቲት 2013 ዓ.ም. ምሽት ላይ የአማራ ሚሊሻ አባላት የሆኑ ወታደሮች እንደሆኑ የምትገምታቸው 9 ወታደሮች በሯን በርግደው ከገቡ በኋላ ጌጣጌጥ እና ገንዘብ እንድትሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ የተባሉትን ያደርጋሉ።
ሦስቱም ባሉበት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላጋጠማቸው የስሜት መቃወስ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ይገልጻሉ።
የአስገድዶ መድፈሩ ዘመቻ በተጀመረባት ትግራይ፤ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አምደስላሴ እንደሚሉት፤ አብዛኛው ወደ ሆስፒታሎች የመጡት የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች ከባድ የሆነ የአእምሮ ጤና መቃወስ ምልክት አሳይተዋል። “ፒቲኤስዲ በጣም የተለመደ ነው። እራስን የማጥፋት ሙከራዎች ነበሩ” ብለዋል።
ሌሎች ደግሞ የድብታ ምልክት እንዲሁም ማንነትን እና ያሉበትን ሁኔታ የመሳት ምልክቶች ያሳያሉ። “አንዳንዶቹ እራሳቸውን አያውቁም። ወደ እብደት ይሄዳሉ” ይላሉ።
የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎችን በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እያከመች ያለችው ነርስ ሉዋም ገ/ስላሴ በበርካታ ታካሚዎቿ ተመሳሳይ መልክቶችን እያስተዋለች እንደሆነ ትገልጻለች። “እራሳቸውን ይነጥላሉ። ሁሉም ሰው ስላጋጠማቸው ነገር የሚያውቅ ይመስላቸዋል።”
ባለፈው ጥቅምት በማይካድራ ከተማ አንዲት የ15 ዓመት ሴት ልጅ በአራት የአማራ ሚሊሻ አባላት ተገዳ ከተደፈረች በኋላ እራሷን ሰቅላ ማጥፋቷን ትናግራለች።
በአሁኑ ወቅት ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸው በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ላሉት ቅድሚያ የሚሰጠው ትኩረት ከአካላዊ እና አዕምሯዊ ቁስላቸው ማገገም ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም የሚስማሙበት አንድ ነገር፤ በቡድን ተገዶ የመደፈር መጥፎ ትውስታ ለመጪው ዓመታት አብሯቸው የሚቆይ ይሆናል።
*የተጎጂዎችን ማንነት ለመጠበቅ ሲባል በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ ስሞች እንዲቀየሩ ተደርገዋል።
ይህ የምርመራ ዘገባ በናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ደጋፍ የተዘጋጀ ነው።
“ባለቤቴ ስለተሆነው የሚያውቀው ነገር የለም። ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ አልተገናኘንም፤ በሕይወት ይኑር፤ ይሙት የማውቀው ነገር የለም።
እንዲያውቅ አልፈልግም።
የተፈጠረውን ሁሉ ረስቼ ወደቀደመ ሕይወቴ መመለስ ነው የምፈልገው።”
– የ39 ዓመት የትግራይ እናት
ሲሲአይጄ የአርትዖት እና ዲዛይን ቡድን
አርትዖት
ሊዲያ ናሙቢሩ
ያፋ ፍሬድሪክ
ዳታ
ሶቲሪስ ሲዴሪስ
ዩክሲ ዋንግ
ዲዛይን እና ቪዡዋል
ጁሊያን ዱዳዚአክ
ስኮት ሌዊስ